1. |
Fiker
05:16
|
|||
ይታየኛል ጎህ ሲቀድ ሲያልፍ ጨለማው
የማለዳው ብርሀን ቀኑን ሲወርሰው
አሻግሬ አያለው አሁን ካለንበት
ተስፋን ስንይዘው ሲሆነን ሕይወት
ቢደክምም ያሁን ልፋት
ቢመስልም ነገ ጥፋት
እውነት ብትደበዝዝ
ባትታይ ደምቃ እንዳልማዝ
ከእቅብ ስር ቢሆን ሻማችን
ፍርሀት ቢሸሽግብን
ግን እንነሳለን ያልፋል ሀዘናችን
እያሪኮ ይፈርሳል ስንመጣበት
ውቅያኖሱ ይከፈላል ስንራመድ
ፀሀይ ትቆማለች ካዘዝናት
ለምን ብትል ምድር ፍቅር ሆነን ምክንያት
ይታየኛል ጎህ ሲቀድ ሲያልፍ ጨለማው
የማለዳው ብርሀን ቀኑን ሲወርሰው
አሻግሬ አያለው አሁን ካለንበት
ተስፋን ስንይዘው ሲሆነን ሕይወት
ቢደክምም ያሁን ልፋት
ቢመስልም ነገ ጥፋት
እውነት ብትደበዝዝ
ባትታይ ደምቃ እንዳልማዝ
ከእቅብ ስር ቢሆን ሻማችን
ፍርሀት ቢሸሽግብን
ግን እንነሳለን ያልፋል ሀዘናችን
እያሪኮ ይፈርሳል ስንመጣበት
ውቅያኖሱ ይከፈላል ስንራመድ
ፀሀይ ትቆማለች ካዘዝናት
ለምን ብትል ምድር ፍቅር ሆነን ምክንያት
እያሪኮ ይፈርሳል ስንመጣበት
ውቅያኖሱ ይከፈላል ስንራመድ
ፀሀይ ትቆማለች ካዘዝናት
ለምን ብትል ምድር ፍቅር ሆነን ምክንያት
|
||||
2. |
Emnet
03:41
|
|||
እስከምድር ጫፍ ተጏዝኩ ስፈልግ
ተስፋን አንግቤ በፅናት
አገኘው ይሆን ወይ የልቤን ጥማት
አውቀውስ ይሆን ወይ ሳገኘው ያን ለት
ብዕሬን ሞጫጨርኩ ማስታወሻዬ ላይ
ባገኘው ብዬ ጥበብ ውስጥ ቢታይ
ሸፍኖትስ ቢሆን የወረቀት ክምር
ገፆቼን ከፈትኩ ባገኘው ከስር
እምነት ተሰውሮብኛል በምናብ ብፈልገው ጠፍቷል
ተራራን ባህር ይከታል የልቤን አለት ግን ማን ይንዳል
እምነት ተሰውሮብኛል በምናብ ብፈልገው ጠፍቷል
ተራራን ባህር ይከታል የልቤን አለት ግን ማን ይንዳል
ቅኔዎችን ሁሉ ዘረፍኩ
የታሪክን ዳራ አሰስኩ
ብዙ ደከምኩ ስበረብር
ግን ወዳጁን ብቻ አገኘው ስራን
አገናኘኝ ብዬ ለመንኩት
ይዞኝም እንዲሄድ ጠየኩት
ተከተለኝ አለኝ ከሗላ
ሊገናኘኝ ከእምነት ጋራ
እምነት ተሰውሮብኛል በምናብ ብፈልገው ጠፍቷል
ተራራን ባህር ይከታል የልቤን አለት ግን ማን ይንዳል
እምነት ተሰውሮብኛል በምናብ ብፈልገው ጠፍቷል
ተራራን ባህር ይከታል የልቤን አለት ግን ማን ይንዳል
እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት
እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት
እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት
እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት
እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት
እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት እምነት
እምነት ተሰውሮብኛል በምናብ ብፈልገው ጠፍቷል
ተራራን ባህር ይከታል የልቤን አለት ግን ማን ይንዳል
እምነት ተሰውሮብኛል በምናብ ብፈልገው ጠፍቷል
ተራራን ባህር ይከታል የልቤን አለት ግን ማን ይንዳል
|
||||
3. |
Tesfa
04:23
|
|||
ማለዳ ይነሳል ዛሬን ለማሸነፍ
ከቤቱም ሲወጣ እንዲ ብሎ ነበር
ፈጣሪዬ ሆይ በቀኝህ አውለኝ
ህይወት እንዳትከዳኝ አቤቱ አስበኝ
ተስፋ አለህ
ተስፋ አለህ
ተስፋ አለህ
ተስፋ አለህ
ከአድማሱ ባሻገር ይታያል ወገግታ
ፀሀይ ልትወጣ ነው አዲስን ቀን ይዛ
ብርሀኗ ቢደበዝዝ በደመና ተሸፍኖ
ማየት ግን አይቀርም ውበቷም ደምቆ
ተስፋ አለህ
ተስፋ አለህ
ተስፋ አለህ
ተስፋ አለህ
|
||||
4. |
Ariob (Acoustic)
03:18
|
|||
ዝም በል በቃ አትናገር ዝም በል በቃ አታውራ
መንገድ የለም ወዲያ ማዶ አልደረስንም ቁም እሱ ጋ
ግን ያየሁት እሩቅ ነው አልችልም መዘግየት
ሀሳቤ ሰፊ ነው ልቀቁኝ ልሂድበት
በወይኒ ውስጥ ሆኖ ይሰማል ጩኸቶ
መንገድ የሚያስጀምር መውጫ በማጣቴ
አልጠብቅም ለሊቱ እስኪለቅ
እንዳርዮብ ልውጣ እና ልድመቅ
ቁጭ በል በቃ እንዳትሄ ቁጭ በል በቃ ባለህበት
እምትለው ገብቶናል ግን ያልከው ቦታ ማን ይደርሳል
ምን አለ ቢተዉኝ እንዳፈርስ አጥሩን
እስከ መቼ ፈርተው ይዘጋሉ ቅጥሩን
በወይኒ ውስጥ ሆኖ ይሰማል ጩኸቶ
መንገድ የሚያስጀምር መውጫ በማጣቴ
አልጠብቅም ለሊቱ እስኪለቅ
እንዳርዮብ ልውጣ እና ልድመቅ
በወይኒ ውስጥ ሆኖ ይሰማል ጩኸቶ
መንገድ የሚያስጀምር መውጫ በማጣቴ
አልጠብቅም ለሊቱ እስኪለቅ
እንዳርዮብ ልውጣ እና ልድመቅ
|
||||
5. |
Niser
03:26
|
|||
ቀስ በቀስ ይራመዳል እንቁላል እግር ያወጣል
የሚኖር ባይመስልም አንድ ቀን ይሄዳል
ቢገርምም ነገሩ ይሆናል ግድ የለም
ከቅፊት ሲወጣ ያስተውላል አለም
መሰል ጫጩቶቹን ያስተባብራል
ለካ ላባ ቢያብር ሽፋን ይሆናል
ክንፉ ያድጋል አንድ ቀን ይበራል
የእግሩን እረስቶ ሰማይ አልሟል
ይበራል እንደ ንስር ይወጣል ከደመናው በላይ
ይበራል እንደ ንስር ፈተናን ሁሉ ቁልቁል ሊያይ
በሮ ወደላይ ነፋስ ይቀዝፋል
ክንፎቹን መቶ ደመና ውስጥ ይገባል
የተዘባበቱበት አይናቸው እያየ
ለይመለስ ከቶ ወደላይ ከፍ አለ
መሰል ጫጩቶቹን ያስተባብራል
ለካ ላባ ቢያብር ሽፋን ይሆናል
ክንፉ ያድጋል አንድ ቀን ይበራል
የእግሩን እረስቶ ሰማይ አልሟል
ይበራል እንደ ንስር ይወጣል ከደመናው በላይ
ይበራል እንደ ንስር ፈተናን ሁሉ ቁልቁል ሊያይ
ይበራል እንደ ንስር
ይበራል እንደ ንስር
|
||||
6. |
Desta
04:00
|
|||
ብቻህን ከምትሄድ ብዙ ሆነኸ ተጏዝ
ያንተን ተሸክመኽ የሌላውንም ያዝ
ከደግነት መንገድ ፊትህን አታዙር
በማማ ላይ ሆነክ በሰዎች ልብ ኑር
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
ሰዎች ሁሉ ልብ ካለ ልግስና
የሚሰጡ እጆች መና አይቀሩምና
ከእጅ ስለጠፋው ከቶ አትማረር
ያጣኸውን ሁሉ እንደሰጠኽ ቁጠር
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
መቆም ስትጀምር የወደቀን አንሳ
ወደፊት ስትሄድ ጀርባህን አትርሳ
እቺ አልቦ አለም ሙሉ እምትሆነው
ያከማቸ ሁሉ ያለውን ሲሰጥ ነው
መቆም ስትጀምር የወደቀን አንሳ
ወደፊት ስትሄድ ጀርባህን አትርሳ
እቺ አልቦ አለም ሙሉ እምትሆነው
ያከማቸ ሁሉ ያለውን ሲሰጥ ነው
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
|
||||
7. |
Zaf ft.Dagy
04:51
|
|||
ተስፋ ተጥሎበት የት ይደርሳል ተብሎ
ኀላፊ አግዳሚው በርሱ ተገርሞ
ባፈራው ቅርንጫፍ ስንቱን አስጠልሎ
ይኖር ነበረ የኖረ መስሎ
ግን ተቆረጠ በሰዎች እጅ ወደቀ
ተስፋ እንዳይኖረውም ተሰነጠቀ
መልሶ እንዳይበቅል ደግሞ እንዳይሆን ጥላ
በቅርንጫፎቹ መጥረቢያ ተሰራ
አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ
ግን ደግሞ ይነሳል አይሞትም እሱ
ያቆጠቁጣ ከሞተው ክፍሉ
መልሶ ይመጣል ውሀን አሽቶ
አብዝቶ ያፈራል ከቀድሞ አብልጦ
መውደቅ እንዳለ አለ ደግሞ መነሳት
ተስፋ አጥቶ ደግሞ ማግኘት መልሳ ተስፋን
አይቀርም ደርቆ አለ መልሶ ማፍራት
ዛሬ የጠፋው ነገ ደግሞ ይበራል
ሰዎች ቢሉት የሞተ የተላቀቀም ቢመስል ከፍጥረት ጎራ
አይመለስ ብለው ለዘላለም አሸልቧል በቃ ለይቷል
ይሰማል መንፈሱ በህይወት ጎዳና ስሙን ሰምቶ ይወጣል
ዳግም አንሰራርቶ ሙታንን ተላቆ (መጣ) ከህያዋን መንደር
ራሱን ሰቶ ለህይወትም ቃና
አሽብርቆ ይታይ የለ ገና
አልጨረሰም አለው አለው ሌላ
በዝቶለታ አለው ገና ገና
ቆሞ ይሄዳል እንዳዲስ ነው ሌላ
ከሞተበት ክፍል መቃብሩ ተከፍቶ ይወጣልና
አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ
አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ
|
Dawit Cherent Ethiopia
Dawit Cherent is an Ethiopian singer/songwriter and producer. After he released his first english EP Humble in 2017, he was known for his distinctive indie sound he brings to the Ethiopian flavor. On 2019 he released his second Amharic EP SEW which was well received by many listeners, and was featured on VOA-music time africa as a young rising talent in africa. ... more
Streaming and Download help
If you like Dawit Cherent, you may also like:
Bandcamp Daily your guide to the world of Bandcamp